APOSTOLIC ETHIOPIAN CHURCH:SONGS WITH LYRICS

Описание к видео APOSTOLIC ETHIOPIAN CHURCH:SONGS WITH LYRICS

እንዲህ አይነት ግሩም ዝማሬ ሰምተን እንድንባረክበት በብዙ መስዋዕትነት ያቀረቡልንን የህብረት መዘምራንን ኢየሱስ እየባረከ ይባርክ።አሜን።
እናንተም ከተባረካችሁበት በኮመንት ላይ ተባረኩ በማለት ከዚህ የበለጠ ፀጋ እንዲበዛላቸው ደግፏቸው።
የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን
APOSTOLIC CHURCH OF ETHIOPIA
watch full video #apostolicsongs #apostolicchurchsongs #ኢየሱስ #nahom terefe #viralvideo


ተሻገር ወደአየልህ

ከሚታየው ነገር ጀርባ ከሚናወጠው
አለ ብዙ መልካም ነገር እግዚአብሔር ያየው
አለ ድል አለ
አለ ምርኮ አለ
አለ ሰላም አለ
እግዚአብሔር ያየው መልካም ነገር አለ

ዛሬ የምታያቸውን ለዘለዓለም ላታያቸው
አንዴ በቅዱስነቱ ላይተውህ በራሱ የማለው
የተናገረህ የታመነው ጌታ
ቀን አይከለክለው አይገደው ሁኔታ
ይልቅ ፊትህ ያለውን ማዕበሉን ትተህ
ተሻገር በመንፈስ ወደታየልህ
አይንህን አንሳና እይ ተመልከት
እንደ አሸዋ እንደከዋክብት
ዘርህን ሊያበዛው ባንተ ውስጥ ያለው
በዚህ ከተማ ብዙ ህዝብ አለው
ቀና በል ወደ አምላክህ ተሻገር ወዳየልህ
ጠጋ በል ከእግሩቹ ስር በእውነት ተስፋ ፍፃሜ አለህ (x2)

ለጊዜው የሚሆነውን የሚታየውን ተውና
የአምላክህ አይኖች አሻግረው ያዩትን ተመልከትና
እርሱን ተከተለው ሀሰት አያውቅም
ከአፉ ያወጣውን ቃል አይለውጥም
እኔ ጋሻህ ብሎ ብቻህን ሲጠራህ
ባንተ ብዙ ዕቅድ አለው ብዙ ስራ

አይንህን አንሳና እይ ተመልከት..........

ማስተዋል የማያውቀው ጥበብ ያልደረሰበትን
የእግዚአብሔር እውቀት መርምሮ ያየውን ብቻ ተመልከት
የእስራኤል ቅዱስ በመሃከልህ ነው
አትፍራ አትደንግጥ ክንዱ ከአንተ ጋር ነው
ወደኃላ አትበል ማራውን አይተህ
ተሻገር በኤሊም ብዙ ምንጭ አለህ
መፈራታቸውን ከቶ አትፍራ
ይሆኑልሃል ልክ እንደእንጀራ
ሂድ ምድሪቱን በዝብዝ ውረሰው
እግዚአብሔር አለ ካንተ ጋራ ነው
ቀና በል ወደ አምላክህ ተሻገር ወዳየልህ
ጠጋ በል ከእግሩቹ ስር በእውነት ተስፋ ፍፃሜ አለህ


Apostolic Songsሀ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке