Logo video2dn
  • Сохранить видео с ютуба
  • Категории
    • Музыка
    • Кино и Анимация
    • Автомобили
    • Животные
    • Спорт
    • Путешествия
    • Игры
    • Люди и Блоги
    • Юмор
    • Развлечения
    • Новости и Политика
    • Howto и Стиль
    • Diy своими руками
    • Образование
    • Наука и Технологии
    • Некоммерческие Организации
  • О сайте

Скачать или смотреть የሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ ገድል (በከፊል)

  • መባ-Mebba
  • 2025-12-12
  • 113
የሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ ገድል (በከፊል)
  • ok logo

Скачать የሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ ገድል (በከፊል) бесплатно в качестве 4к (2к / 1080p)

У нас вы можете скачать бесплатно የሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ ገድል (በከፊል) или посмотреть видео с ютуба в максимальном доступном качестве.

Для скачивания выберите вариант из формы ниже:

  • Информация по загрузке:

Cкачать музыку የሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ ገድል (በከፊል) бесплатно в формате MP3:

Если иконки загрузки не отобразились, ПОЖАЛУЙСТА, НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если у вас возникли трудности с загрузкой, пожалуйста, свяжитесь с нами по контактам, указанным в нижней части страницы.
Спасибо за использование сервиса video2dn.com

Описание к видео የሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ ገድል (በከፊል)

ታኅሣሥ 4-ሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ ዕረፍቱ ነው፡፡ እንድርያስ ማለት ‹‹ጽኑ በኩር›› ማለት ነው፡፡ ሐዋርያው እንድርያስ የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስ ወንድም ሲሆን በመጀመሪያ የተጠራ ሐዋርያ ነው፡፡ በመጀመሪያ የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር የነበረ ቢሆንም መጥምቁ የጌታችንን መንገድ ሲጠርግና ስለ ክርስቶስም ሲሰብክ ስለሰማው በዚያው የጌታችን ደቀ መዝሙር ሆኗል፡፡ ከሰው ጋር ፈጥኖ የመግባባት ችሎታ ስለነበረው በሐዋርያትም ዘንድ እንደ አስተባባሪ ይቆጠር ነበር፡፡ ጌታችን 5 እንጀራና ሁለቱን ዓሣ አበርክቶ ሕዝቡን ሲመግብ እንጀራውንና ዓሣዎቹን የያዘውን ወጣት ወደ ጌታችን ወስዶ እንዲባረክ ያደረገው እንድርያስ ነው፡፡ በዚህም የወጣቶች ሐዋርያ እየተባለ ይጠራል፡፡
ሐዋርያው በሩሲያ፣ በቢታንያ፣ በገላቲያና በሩማንያ ወንጌልን ሰብኮ ብዙ ክርስቲያኖችን አፍርቷል፡፡ የቍስጥንጥንያ የመጀመሪያው ሊቀ ጳጳስ ነው፡፡ በግሪክ ሲያስተምር ከሃዲያን ይዘው በ60 ዓ.ም ታኅሣሥ 4 ቀን ሰቅለው ገድለውታል፡፡ ሊሰቅሉት ሲወስዱትም ‹‹ጌታዬ በተሰቀለበት ዓይነት መስቀል አትስቀሉኝ›› በማለት ሲለምናቸው እነርሱም ፍቃዱን ፈጽመውለት የእንግሊዝኛውን ኤክስ (X) ፊደል ቅርጽ ባለው መስቀል ላይ ሰቅለውታል፡፡ ስኮትላንዶች የቀኝ የእጆቹን ጣቶች በአንድ መነኩሴ አማካኝነት ስላገኙ ሐዋርያው እንድርያስን ‹‹ጠባቂያችን›› ነው እያሉ ይመኩበታል፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ ወንጌልን እየሰበከ በጽርዕ አገር ሳለ ክብር ይጋበውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፡- ‹‹ሰውን የሚበሉ ሰዎች ማትያስን ይዘው አሥረውታል፣ ከሦስት ቀንም በኋላ ሊበሉት ከእሥር ቤታቸው ያወጡታልና አንተ አሁን ወደ እነዚያ ሰውን ወደሚበሉት ሰዎች አገር ሂድ›› አለው፡፡ እነዚህም ሰውን ስለሚበሉት ሰዎች ለማወቅ ካስፈለገ የሐዋርያውን የማትያስን ገድል መመልከቱ ተገቢ ነው፡፡ ወይም በቅድስት ‹‹ፍቅርተ ክርስቶስ›› ገድል ላይም በስፋት ተጠቅሷል፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ማትያስ በአስቆሮቱ ይሁዳ ምትክ ከተተካ በኋላ ሰውን ወደሚበሉ ሰዎች አገር ሄዶ ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ ዕጣ ደረሰው፡፡ ይህችም ሀገር እስኩቴስ የተባለች የሩሲያ ክፍል እንደሆነች የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች ተናግረዋል፡፡ ማትያስም እነዚህ ሰውን የሚበሉ ሰዎች አገራቸው እንደደረሰ ዐይኑን አውልቀው አሠሩት፡፡ ምግባቸውም የመጻተኛ ሰው ሥጋ ነው፡፡ በልማዳቸው መሠረት መጻተኛን ሰው ገና እንደያዙት ዐይኖቹን ዐውልቀው በእሥር ቤት ያኖሩታል፡፡ እስከ 30 ቀንም ድረስ ሳር እያበሉ ያስቀምጡትና በ30ኛው ቀን ከእሥር ቤታቸው አውጥተው አርደው ይበሉታል፡፡ ሐዋርያው ማትያስንም እንደሥርዓታቸው ዐይኖቹን አውልቀው አሥረውት ሳለ 30ኛው ቀን ሳይፈጸም ነው ጌታችን ለሐዋርያው እንድርያስ ተገልጦለት ሄዶ ማትያስን እንዲያድነው የነገረው፡፡ ጌታችን ለእንድርያስ ተገልጦለት ‹‹ሰውን የሚበሉ ሰዎች ማትያስን ይዘው አሥረውታል፣ ከሦስት ቀንም በኋላ ሊበሉት ከእሥር ቤታቸው ያወጡታልና አንተ አሁን ወደ እነዚያ ሰውን ወደሚበሉት ሰዎች አገር ሂድ›› ባለው ጊዜ እንድርያስም መልሶ ጌታችንን ‹‹ጌታዬ ፈጣሪዬ የወረው ሦስት ቀን ከሆነ እንዴት እደርሳለሁ? ነገር ግን ፈጥኖ የሚያወጣውን ከመላእክት አንዱን ላክ እንጂ›› አለው፡፡ ጌታችንም ‹‹እኔ ሀገሪቱን ራሷን ወደዚህ ነይ ካልኳት በውስጧ ከሚኖሩት ሁሉ ጋር ትመጣለች፤ አሁን ግን ፈቃዴ አንተና ደቀ መዝሙሮችህ እንድትሄዱ ነውና ነገ በጠዋት ተነሥታችሁ ወደ ባሕሩ ሂዱ የተዘጋጀች መርከብም ታገኛላችሁ›› አለው፡፡ ጌታችን ለእንድርያስ ይህንን ከነገረው በኋላ በክብር ዐረገ፡፡
በነጋም ጊዜ እንድርያስ ከቀደ መዝሙሮቹ ጋር ተነሥቶ ወደ ወደቡ ደረሰ፡፡ ጥሩ የተዘጋጀች መርከብንም አገኘ፡፡ ጌታችንም በሊቀ ሐመር አምሳል ተገለጠለት ነገር ግን እንድርያስ አላወቀውም ነበርና ‹‹ሊቀ ሐመር ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን!›› አለው፡፡ ጌታችንም ‹‹የእግዚአብሔር ሰላም ይደርብህ›› አለው፡፡ እንድርያስም ‹‹በዚህ መርከብ ወዴት ትሄዳለህ?›› ሲለው ጌታችንም ‹‹ሰውን ወደሚበሉ ሰዎች አገር እሄዳለሁ›› አለው፡፡ እንደርያስም ‹‹ወንድሜ ሆይ! ከአንተ ጋራ ትጭነኝ ዘንድ እለምንሃለሁ›› አለው፡፡ በሊቀ ሐመር አምሳል የተገለጠው ጌታችንም ወደ መርከቡ ካወጣቸው በኋላ ሲጓዙ እንድርያስን ‹‹ጌታህ ምን ኃይል አደረገ?›› አለው፡፡ እንድርያስም ‹‹ጌታችን ያደረጋቸውን ተአምራቶች ሊነግረው ጀመረ የሚያናግረው ራሱ ጌታችን መሆኑን አላወቀም ነበርና፡፡ ከዚህም በኋላ ሊቀ ሐመሩ እንደሚያንቀላፋ ሰው ሆነ፣ ያንጊዜም እንድርያስና ደቀ መዝሙሮቹ ተኙ፡፡ ወዲያውም ጌታችን እንድርያስንና ደቀ መዝሙሮቹን ይሸከሟቸው ዘንድ መላእክትን አዘዛቸውና ወስደው በባሕሩ ዳርቻ አስቀመጧቸው፡፡ ከእንቅልፋቸውም በነቁ ጊዜ መርከብን አላገኙም፡፡ እንድርያስም የመርከቡ ሊቀ ሐመር ጌታችን መሆኑን አሁን ዐወቀና ለልጆቹ ነገራቸው፡፡
እንድርያስም ወዲያው መጸለይ ሲጀምር አሁንም ጌታችን ተገለጠለትና ‹‹ወዳጄ እንድርያስ ሆይ አትፍራ እኔ ይህን አድርጌያለሁና ምንም የሚሳነኝ ነገር እንደሌለ ታውቃለህ፤ አሁንም ወደ እሥር ቤቱ ሄደህ ማትያስንና ከእርሱ ጋር ያሉትን ሁሉ አውጣቸው›› አለው፡፡ እንድርያስም ልጆቹን ይዞ ወደ ከተማው በመግባት ማትያስ ወደታሰረበት ወህኒ ቤት ሲሄድ የወህኒ ቤቱ በሯ ራሷ ተከፈተችለት፡፡ ማትያስንና ደቀ መዝሙሮቹንም በወህኒ ቤቱ ውስጥ አገኛቸውና ሰላምታ ከተሰጣጡ በኋላ ብዙ አወሩ፡፡
እንድርያስም ማትያስን ‹‹ከ2 ቀን በኋላ አውጥተው እንደ እንስሳ አርደው ይበሉኛል አልክ፣ አንተ በጌታችን ዘንድ ያየናትን ያችን ምሥጢር ረሳሃትን? በምናገራት ጊዜ ሰማይና ምድር ይናወጣሉኮ›› አለው፡፡ ማትያስም ‹‹ጌታችንም እንደበጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ ብሏልና ወደዚህ እሥር ቤት በጨመሩኝ ጊዜ ጌታችን ተገልጦልኝ አንተ መጥተህ እንደምታደነኝ ገልጦልኛልና አሁንም የምታደርገውን አስተውል›› አለው፡፡ እንድርያስም ወደ እሥረኞቹ በተመለከተ ጊዜ እንደ እንስሳ ሣር ሲበሉ አይቶ እጅግ በማዘን አለቀሰ፣ ሰይጣንንም ከሠራዊቱ ጋር አሠረው፡፡
ከዚህም በኋላ ሁለቱ ሐዋርያት ተነነሥተው ከጸለዩ በኋላ እጆቻቸውን በእሥረኞቹ ላይ ጫኑባቸውና ወደ አእምሮአቸው መለሷቸው፡፡ ከከተማውም ወጠተው በዚያ በአንድነት እንዲቀመጡ አዘዟቸውና ወጥተው በከተማው ጎዳና ዳር ተቀምጠው የሚሆነውን መከታታል ጀመሩ፡፡ ሰውን የሚበሉት የሀገሪቱ ሶችም እንደልማዳቸው የሚበሉትን ተረኛ ሰው ከእሥር ቤቱ ሊያወጡ ሲመጡ የእሥር ቤቱ በር ተከፍቶ እሥረኞቹም አምልጠው መውጣታቸውን ተመለከቱ፡፡ በዚህም ጊዜ ሰይጣን ሰውን መስሎ ተገለጠላቸውና ‹‹ይህንን ያደረጉት ሐዋርያት ናቸው›› አላቸው፡፡ እነርሱም ሁለቱን ሐዋርያት ይዘው በማሠር በከተማ እየጎተቱ አዞሯቸው፡፡ በእሥር ቤትም እያሳደሩ እስከ ሦስት ቀን እንዲሁ አደረጉባቸው፡፡ ደማቸውም በምድር ላይ እንደውኃ ፈሰሰ፡፡ እንድርያስና ማትያስም ጸሎት ካደረጉ በኋላ አንድን የእምነ በረድ ምሰሶን ከሥሩ የጥፋት ውኃን አፍልቆ ከተማዋን ያጥለቀልቃት ዘንድ አዘዙት፡፡ እንዳዘዙትም ከእምነ በረዱ ምሰሶው ሥር ብዙ ውኃ ፈልቆ የከተማዋን ሰዎች ያሰጥማቸው ዘንድ ገነፈለ፡፡ የአገሪቱም ሰዎች ሸሽተው ከከተማው ለመውጣት ቢሞክሩም ውኃ እስከ አንገታቸው ድረስ አስጥሞ ያዛቸው፡፡ ብዙዎቹም ሞቱ፡፡ ከዚህም በኋላ ‹‹ወዮልን ወዮታ አለብን፣ ይሄ ሁሉ የደረሰብን በእነዚያ በተመረጡ ሰዎች ላይ ምክንያት ነው እኛም በአምላካቸው እናምናለን›› አሉ፡፡
እንድርያስም ከዚህ በኋላ ውኃውን እንዲጎድል አዘዘውና እንዳዘዘው ጎድሎ ጠፋ፡፡ የአገሪቱም ሰዎች ወደ ሐዋርያት ቢመጡ ሐዋርያቱን ቆመው ሲጸልዩ አገኟቸውና ‹‹ይቅር በሉን›› ብለው ለመኗቸው፡፡ ሐዋርያትም ‹‹በሕያው እግዚአብሔር እመኑ እንጂ አትፍሩ›› አሏቸው፡፡ እንድርያስና ማትያስም ዳግመኛ ወደ ጌታችን ጸልየው በውኃው ስጥመት የሞቱትን በርካታ ሰዎች ከሞት እንዲነሡ አደረጓቸው፡፡ ሰውን የሚበሉትን የአገሪቱንም ሰዎች ሁሉ አእምሮአቸውንና የቀድሞ አርያቸውን መለሱላቸው፡፡ አስቀድሞ ሰይጣን አድሮባቸው ነበርና፡፡ አሁን ግን የቀድሞው የአራዊት ጸባያቸውም ርቆላቸው ሰው የሚበላውን ምግብ የሚመገቡ የዋሆች ሆኑ፡፡ ከዚህም በኋላ ሁለቱ ቅዱሳን ሐዋርያት ሁሉንም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው፡፡ ሥጋ ወደሙንም አቀበሏቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ሠርተውላቸው ሕግና ሥርዓትን ሁሉ አስተምረው ከትእዛዛቸው እንዳይናወጹ መክረዋቸው የቀናች ሃይማኖትን አጸኑላቸው፡፡ ሐዋርያትም ሃይማኖትን እያስተማሯቸው 30 ቀን አብረዋቸው ከተቀመጡ በኋላ አገልጋይ ኤጲስ ቆጶሳትን፣ ካህናትንና ዲያቆናትን ሾሙላቸው፡፡ የከበሩ ቅዱሳን ሐዋርያት ብዙ ተአምራትን አደረጉ፣ ሕሙማንን ሁሉ ፈወሱ፡፡ ከዚህም በኋላ እንድርያስ ከደቀ መዝሙሮቹ ጋር ወደ ግሪክ አገር ተመለሰ፡፡
የሐዋርያው የቅዱስ እንድርያስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!

✞ ✞ ✞
#eotc #tewahedo #ethiopia #habesha #duet #love #greenscreen #orthodox

Комментарии

Информация по комментариям в разработке

Похожие видео

  • የታኅሣሥ ገድለ ቅድስት አርሴማ
    የታኅሣሥ ገድለ ቅድስት አርሴማ
    2 месяца назад
  • የታኅሣሥ ድርሳነ ገብርኤል/Archangel Saint Gabriel
    የታኅሣሥ ድርሳነ ገብርኤል/Archangel Saint Gabriel
    2 месяца назад
  • ብርሃን ሆነ ጨለማ ተገፈፈ //Yelelit haylenga tislot // Night time prayer #fastingprayer #prayer #motivational
    ብርሃን ሆነ ጨለማ ተገፈፈ //Yelelit haylenga tislot // Night time prayer #fastingprayer #prayer #motivational
    1 день назад
  • ቃለ እግዚአብሔር|| ገድለ ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ|| ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ(ታኅሣሥ 4)
    ቃለ እግዚአብሔር|| ገድለ ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ|| ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ(ታኅሣሥ 4)
    1 год назад
  • ገድለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
    ገድለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
    2 месяца назад
  • የየካቲት 2 ሥንክሳር#የአባ ጳውሊ ዕረፍት#አባ ሕርያቆስ#ሐዋርያት ቶማስና ታዴዎስ#ፃድቁ ኢዮብ#አቤል የዋህ
    የየካቲት 2 ሥንክሳር#የአባ ጳውሊ ዕረፍት#አባ ሕርያቆስ#ሐዋርያት ቶማስና ታዴዎስ#ፃድቁ ኢዮብ#አቤል የዋህ
    3 недели назад
  • ገድለ ፊሊጶስ ሐዋርያ
    ገድለ ፊሊጶስ ሐዋርያ
    3 месяца назад
  • የዓርብ ገድለ አቡነ ሃብተ ማርያም
    የዓርብ ገድለ አቡነ ሃብተ ማርያም
    2 месяца назад
  • የጥር  4 የነባቤ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ገድል
    የጥር 4 የነባቤ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ገድል
    1 месяц назад
  • ጥምቀት/Epiphany
    ጥምቀት/Epiphany
    1 месяц назад
  • ኅዳር ፰/8 በዓለ አርባዕቱ እንስሳ
    ኅዳር ፰/8 በዓለ አርባዕቱ እንስሳ
    3 месяца назад
  • የኅዳር ድርሳነ ሚካኤል
    የኅዳር ድርሳነ ሚካኤል
    3 месяца назад
  • የጥር ድርሳነ ዑራኤል- Archangel St Urael
    የጥር ድርሳነ ዑራኤል- Archangel St Urael
    1 месяц назад
  • የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት - The Birth of Jesus Christ
    የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት - The Birth of Jesus Christ
    1 месяц назад
  • የቅዱስ እንድሪያስ ታሪክ /The story of saint Andrew
    የቅዱስ እንድሪያስ ታሪክ /The story of saint Andrew
    4 года назад
  • ገድለ ቅዱስ ሚናስ
    ገድለ ቅዱስ ሚናስ
    3 месяца назад
  • ገድለ አቡነ ዘርዓ ቡሩክ
    ገድለ አቡነ ዘርዓ ቡሩክ
    1 месяц назад
  • ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት - The Birth of Saint Tekle Haymanot
    ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት - The Birth of Saint Tekle Haymanot
    2 месяца назад
  • ሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ | ገድል ድርሳን ስንክሳር
    ሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ | ገድል ድርሳን ስንክሳር
    2 месяца назад
  • የጥር ገድለ አቡነ አረጋዊ
    የጥር ገድለ አቡነ አረጋዊ
    1 месяц назад
  • О нас
  • Контакты
  • Отказ от ответственности - Disclaimer
  • Условия использования сайта - TOS
  • Политика конфиденциальности

video2dn Copyright © 2023 - 2025

Контакты для правообладателей video2contact@gmail.com